s-801
| ወታደርም ባለቅኔም ነው ። |
s-802
| ይህ አልጋም መቀመጫም ይሆናል ። |
s-803
| ስሕተቱ የኔም ያንተም ነው ። |
s-804
| ከዚህም ትንሽ ልውሰድ ? |
s-805
| ዓለሙ ከሄደ ተስፋዬም ይሄዳል ። |
s-806
| አምስቱም ተበላ ። |
s-807
| ስንዴ እህል ነው ፣ ገብስና ጤፍም እንዲሁ ። |
s-808
| እርሱም ደግሞ ይሄዳል ። |
s-809
| ማንበብም መጻፍም አይችልም ። |
s-810
| ጊዜም ሆነ ገንዘብ የለኝም ። |
s-811
| አንተ ካልመጣህ እሱም አይመጣም ። |
s-812
| እሱም አያውቀውም ። |
s-813
| ኃይሉ መምጣት አይችልም እኔም እንዲሁ ። |
s-814
| አያታችን በዕድሜ እየገፉ ቢሄዱም ለዛቸው አልጠፋም ። |
s-815
| ምግቡ ጥሩ ባይሆንም ራባቸውንን አስታገሠልን ። |
s-816
| የትም ብትሄድ ለኔ ደብዳቤ መጻፍ አትርሳ ። |
s-817
| ይህማ ቢሆን መልካም ነው ። |
s-818
| አስር ዓመት ቢፈጅም ትምህርቴን እጨርሳለሁ እንጂ ወደ ሀገሬስ አልመለስም ። |
s-819
| እንግዲያስ እመጣለሁ ። |
s-820
| ከኛ ጋር እንደምትቆይ መቼስ የታወቀ ነው ። |
s-821
| ምንስ ቢሆን ትመታታለህ ? |
s-822
| ሚስቱስ ብትሆን ጎበዝ ገበሬ ናት ። |
s-823
| ወደ አባትሽ ቤት ብትመለሽስ ? |
s-824
| በእግራችን እንሂድ ወይስ ባውቶቢስ ? |
s-825
| ይህሳ ምንድን ነው ? |
s-826
| ብዙዎችን ለማስተማርሳ ምን ዘዴ አገኛለሁ ? |
s-827
| እግዚአብሔር ሰውን በአምሳሉ ፈጠረ ። |
s-828
| በእውነት አንተን ምን እንደማደርግ አላውቅም ። |
s-829
| ቁርሱን ዳቦ ይበላል ። |
s-830
| ብርጭቆውን ወተት ጠጣበት ። |
s-831
| ሙግቴን ተረታሁ ። |
s-832
| ዐሥር~አለቃው ባለመታዘዙ ማዕረጉን ተገፈፈ ። |
s-833
| ልጁን ቤቱን አሳየው ። |
s-834
| ተራራውን መውጣት ብዙ ጥረት ይጠይቃል ። |
s-835
| እሱን ብሆን አላደርገውም ነበር ። |
s-836
| ጥሩ ሞትን ሞተ ። |
s-837
| ራቁቱን ተኛ ። |
s-838
| ለግብዣ ብቻውን መጣ ። |
s-839
| ባዶ~እጁን መጣ ። |
s-840
| ደረቁን አትብላ ! |
s-841
| ቢላው በቀለን እጁን ቆረጠው ። |
s-842
| ሜዳ ሜዳውን ሄደ ። |
s-843
| እባክህ ወንድም የዚህ ቦታ ስም ማን ይባላል ? |
s-844
| እነሆ ልጄ ፈተናውን በከፍተኛ ውጤት አለፈ ። |
s-845
| ፈተናውን በማለፍህ እንኳን ደስ ያለህ ! |
s-846
| የሷ ጠላ እንዲህ ነው እንዴ ? |
s-847
| ለምን እንደሆነ እንጃ ባየሁት ቁጥር ቱግ እላለሁ ። |
s-848
| የትምህርቱን አስፈላጊነት እንዴት እንደምገልጽ እንጃልኝ ። |
s-849
| አባትህ የመጣ እንደሆነ እንጃልህ ! |
s-850
| ልጅቷ እኮ ቆንጆ ናት ። |
s-851
| አዬ እባክህ ምንም አልተሻለውም ። |
s-852
| እፎይ ይኸው በመጨረሻ ደረስን ። |
s-853
| ይህ ጉዳይ እጅግ አሳሳቢ ነው ። |
s-854
| ከሳሾቻችን በቀጠሮ አልቀረቡም ። |
s-855
| ላባቱ ታዛዥ ነበር ። |
s-856
| ይህ መንግስት የሕዝቡን ፍላጎት ካላሟላ አንድ ቀን ወዳቂ ነው ። |
s-857
| ይቺ ሴትዮ እህል ካልበላች ሟች ናት ። |
s-858
| ይቺ አሮጌ መኪና ተሰባሪ ናት ። |
s-859
| ቤትህን ሳትቆልፍ እየሄድክ አንድ ቀን እቃህ ሁሉ ተወሳጅ ነው ። |
s-860
| ወረቀቱ በቀላሉ ተቀዳጅ ነው ። |
s-861
| ተፈላጊው የት አለ ? |
s-862
| የከብታችን መሰረቅ በጣም አሳዘነን ። |
s-863
| ሕፃን መምታት የጭካኔ ድርጊት ነው ። |
s-864
| በውትድርና ሙያ ለበላይ ታዛዥ መሆን የግድ ነው ። |
s-865
| በጊዜ መተኛት መብትህ ነው ። |
s-866
| ፈተና መውደቄ አበሳጨኝ ። |
s-867
| ባስፈራራውም ትእዛዜን መጣሱን ቀጠለ ። |
s-868
| መቀለድና መቀባጠርን ይወዳል ። |
s-869
| ቀይ ሹራብ መልበሴን አልወደደችውም ። |
s-870
| መጽሐፉን መስረቁን አመነ ። |
s-871
| በሩን መቀርቀር ረሳ ። |
s-872
| አባያውን በሬ ትተህ ምነው ደህናውን መግረፍህ ? |
s-873
| ምግብ እያለ ምነው አለመብላትህ ? |
s-874
| ሌቱን ሙሉ ስሠራ መቆየቴን አላወቀችም ። |
s-875
| ልጃቸው በጦርነት ላይ መሞቱን ተረዱ ። |
s-876
| ልጁ ሱቁን መዝረፉን በተናዘዘ ጊዜ እናቱ በጣም አዘነች ። |
s-877
| ቤት መሥራት ይችላል ። |
s-878
| ነገ የምትመጣ መሆኑን ሰምቻለሁ ። |
s-879
| መኪና በየጊዜው ካልታደሰ ብዙ የማይቆይ መሆኑ የታወቀ ነው ። |
s-880
| መምጣት መቅረቱን ለማወቅ እፈልጋለሁ ። |
s-881
| የሱ አዲስ አበባ መሄድ አይጠቅመንም ። |
s-882
| ፈተና ለማለፍ በርትቶ ማጥናት ። |
s-883
| ከዚህ የሚብስ ጊዜ አለ ማለት ነው ? |
s-884
| ምን ማለትህ ነው ? |
s-885
| ሚስቱን በመግደል ተከሰሰ ። |
s-886
| አስተማሪው በጣም በመድከሙ ነቅቶ መቆየት አልቻለም ። |
s-887
| አቧራ እንዳይነካው በማለት ሥዕሉን በጨርቅ ሸፈኑት ። |
s-888
| መጽሐፉን ሳይጠይቅ ከመውሰዱ በቀር ምን አደረገህ ? |
s-889
| ከመሄድ ይልቅ ብቆይ ይሻላል ። |
s-890
| ከመምጣቱ ገበታ ላይ ጉብ አለ ። |
s-891
| በሩን ከማለፉ ጩኸት ሰማ ። |
s-892
| ብዙ ጨኸት ከመኖሩ የተነሣ ሊተኙ አልቻሉም ። |
s-893
| በዛሬ ጊዜ ገንዘብ ለማግኘት ሲባል እስከ መግደል ይደረሳል ። |
s-894
| ለመጋባት ስለ መወሰናቸው የሰማሁት ነገር የለም ። |
s-895
| የቦርዱ አባል እንደ መሆኑ ሁሉ የወር ገቢው ከመደበኛ ደሞዙ ዕጥፍ ነበር ። |
s-896
| ዕንጨት ሲረጥብ እንደ መነፋት ይላል ። |
s-897
| ጉሮሮው እንደ መድረቅ ብሏል ። |
s-898
| ጽጌረዳው እንደ ማበብ ብሎ ጠወለገ ። |
s-899
| አስተማሪን አለማክበር ኀጢአተኛ እንደ መሆን ይቆጠራል ። |
s-900
| ሥራው ወደ ማለቁ ነው ። |