Dependency Tree

Universal Dependencies - Amharic - ATT

LanguageAmharic
ProjectATT
Corpus Parttest
AnnotationEphrem, Binyam; Arutie, Gashaw; Woldemariam, Tsegay; Navarro Horñiacek, Juan Ignacio

Select a sentence

Showing 402 - 501 of 1074 • previousnext

s-402 እስከ ነገ ብትቆይስ ?
s-403 ቢያዳምጣትስ ኖሮ
s-404 ዛሬሳ ምንም ምግብ አትቀምስም ?
s-405 ዛሬ ወደ ተማሪ ቤት ለመሄድ አልተሰናዳህምሳ ?
s-406 መስኮቱን ዝጋ !
s-407 እሳቱን ከሰል ጨምርበት !
s-408 ጤናዎንስ እንደምን ነዎት ?
s-409 ወተቱን ምን ያደርጉታል ?
s-410 እኔን ይሰረቃል ብሎ መጠርጠር ዘበት ነው
s-411 ሻንጣዬን ተሰረቅሁ
s-412 ራሱን ከተመታ ወዲህ ማስታወስ አቃተው
s-413 ለልጁ ቤቱን አሳየው
s-414 መሬት ፀሐይን ትዞራለች
s-415 ሀምሌትን ሆኖ የሚጫወተው ማነው ?
s-416 ረኃብ ካዋቂ ይልቅ ልጅን ነው የሚርብ
s-417 ውሸታቸውን ነው
s-418 ፈረሱ ሌጣውን ጋለበ
s-419 ጦማቸውን ዋሉ
s-420 መንገድ ሲያቋርጡ ልጁን እጁን ያዘችው
s-421 ቀኑን ሙሉ ተኝቶ ነበር
s-422 እግዚአብሔርን ! እውነት ነው
s-423 ምን እባክህ ዝናብ እምቢ ብሎ አዝመራው አልተሳካም
s-424 እርሳሱን እንሆ !
s-425 ብድር ነው እንዴ የሚፈልጉት ?
s-426 ይመጣል እንዴ ?
s-427 ይህ ልጅ መዳኑን እንጃ ?
s-428 የዘንድሮን ነገር እንጃልኝ
s-429 እኔ እኮ ይህ ፈረስ ያንተ መስሎኝ ነበር
s-430 አዪ እሱ እዚህ ቢሆን ኖሮ
s-431 ኤዲያ ! ተመልከት ምን እንዳደረግህ
s-432 ፈረሱ ቶሎ ቶሎ ሂያጅ ነው
s-433 ለሚያስፈልገኝ ነገር ሁሉ ደጋፊዬ እሱ ነው
s-434 ገንዘብ ፈላጊ ነኝ
s-435 ይህ ቤት ፈራሽ ነው
s-436 አባቷ ዛሬ ደራሽ ነው
s-437 ሰው ሟች ነው
s-438 ሰው ተሰባሪ ነው
s-439 ጦርነቱ ካልቆመ ሁላችንም ተሰዳጅ ነን
s-440 ዓለሚቱ ተወዳጅ ጠባይ አላት
s-441 ከብታችንን በመስረቁ ምክንያት ታሰረ
s-442 መግደል ኃጢያት ነው
s-443 የልጃቸው መፈታት ሲሰማ ቤታቸው ውስጥ ደስታ ሆነ
s-444 ያለ ፓስፖርት ወደ ውጭ አገር መጓዝ አይቻልም
s-445 ምንም ጐበዝ ቢሆን መሸነፉ አይቀርም
s-446 ፍየል ከመድረሷ ቅጠል መበጠሷ
s-447 እናቲቱ የልጇን ፈተና መውደቅ ሰማች
s-448 አዳዲስ ልብስ መልበስ ይወዳል
s-449 ቤቱ ሊሄድ ሲል ይዘንብ ጀመረ
s-450 ልጁ ከመፍራቱ የተነሣ መርፌውን ሊወጋ አልደፈረም
s-451 የገዛ ልብሴን የመስፋት ችሎታ ምነው በኖረኝ
s-452 ካንዱ አገር ወዳንዱ አገር እየዞርኩ እኖራለሁ
s-453 ሥራው እሰከ ተሠራ ድርስ ግድ የለኝም
s-454 መጥቶ እንደሆነ ግባ በለው
s-455 ልጆቹ ስራ እንዲሰሩ ይደረጋል
s-456 ስትገባ ሰው አይተሃል ?
s-457 ባያጠና ይሻለው ነበር
s-458 በምንም ዐይነት ብትሠራው አለቅየው አይደሰትም
s-459 በእናቴ ፈንታ ምነው እኔ በሞትኩ
s-460 ዳኛውን ፈርቶ ሳይመጣ ቀረ
s-461 እጅህን ሳትታጠብ አትብላ
s-462 እየበላ አነበበ
s-463 እናቱን በማየቱ በጣም ደስ አለው
s-464 ወንድሜ ከአገር~ቤት ስለመጣ ላየው ሄድኩ
s-465 ሳይጨልም ብትመለስ ይሻላል አለዚያ ትጠፋለህ
s-466 ባገኘኋት ቁጥር ሰላምታ ትሰጠኛለች
s-467 በሽርሽር ላይ ሆነን ቢዘንብስ ?
s-468 ስለታመመ አልመጣም
s-469 ተናጋሪው ንግግሩን ቶሎ ቢጨርስ ጥሩ ነበር
s-470 ጓደኞችህ እዚህ ሳይመጡ ቢቀሩስ ?
s-471 መታመሙን እንደነገረኝ መጣሁ
s-472 ባለማጥናቱ ፈተናውን ወደቀ
s-473 የኢኮኖሚው ውድቀት የማይቀር ነው እንበል
s-474 የትኛውንም ብትመርጥ እገዛዋለሁ
s-475 ቤት ብትውል ይሻላል
s-476 ብዙ በመሮጤ እግሬን አመመኝ
s-477 ወደ አባትሽ ቤት ብትመለሽ አይሻልሽምን ?
s-478 ካሳ የአስቴር ወደ ጎንደር መሄድ ሰምቶአል
s-479 ዛሬ ዋና ባትሄድ ይሻልሃል
s-480 ምን ቢሆን ይሻላል ?
s-481 ወደ አገር ቤት በሄድኩ ጊዜ ማንንም አልጠየኩም
s-482 ካሳ አስቴር ወደ ጎንደር መሄድዋን ሰምቶአል
s-483 ካሳ አስቴር ወደ ትምህርት ቤት ስለሄደች ተደሰተ
s-484 ይህ ምስኪን ምነው በደንብ በልቶ አይቼው
s-485 እዚያ ብሆን እመኛለሁ
s-486 ምንም ቢመጣ አልፈራም
s-487 የትም ብትሆን ለኔ ደብዳቤ መጻፍ አትርሳ
s-488 እዚህ ካላችሁ ዘንድ ይህንን ጉዳይ ብንነጋገርበት መልካም ነው
s-489 በጣም ብወድሽም አላገባሽም
s-490 ምነው ቢያዳምጣት ኖሮ
s-491 ሁለት ሰዓት ሳይበላ ቢቆይ ሆዱን አመመው
s-492 ምነው ይህን ያህል ባልሠራ
s-493 ምነው አስተማሪ በሆንሁ
s-494 ገንዘብ ይስጠኝ እንጂ የፈለገውን እገዛለታለሁ
s-495 ገነዘብ ብለምነው አባረረኝ
s-496 አስቴር ወደ ጎጃም ስለ ሄደ አለቀሰች
s-497 እንግዶች ስለማይመጡ ጠላውን አትቅጂ
s-498 ምናልባት ይህን መጽሐፍ ለማሳተም የምትፈልጉ ከሆነ እልካለሁ
s-499 ዘለለ
s-500 ልጁ ወደቀ
s-501 መሬቱ ተንቀጠቀጠ

Text viewDownload CoNNL-U